Skip to main content

በዓለምና በአገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ እየተስፋፋ ያለውን ወቅታዊውን የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምክንያት በማድረግ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ

01.04.2020 Media info Top news
በዓለምና በአገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ እየተስፋፋ ያለውን ወቅታዊውን የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምክንያት በማድረግ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ

በዓለምና በአገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ እየተስፋፋ ያለውን ወቅታዊውን የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምክንያት በማድረግከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ

በዓለምና በአገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ እየተስፋፋ ያለውን
ወቅታዊውን የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምክንያት በማድረግ

በዓለም ላይ ተስፋፍቶ የቆየውና በአሁኑ ጊዜ በአገራችን ኢትዮጵያ የገባው የኮረና ቫይረስ በሽታ ዕለት ዕለት እየተስፋፋ ጥቂት የማይባሉ ወገኖቻችን በወርሽኙ መያዛቸው ታውቋል፡፡

በመሆኑም ይህ ወረርሽኝ እንዳይስፋፋና በቀጣይም ሌሎች ወገኖቻችን እንዳይያዙ መከላከሉ ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ በመሆኑ ቋሚ ሲኖዶስ በዛሬው ዕለት ስብሰባ በማድረግ የሚከተለውን ውሳኔ አሳልፏል፡፡

1. በአሁኑ ጊዜ እየደረሰ ያለው የወረርሽኝ በሽታን አስመልክቶ ከሚመለከታቸው ባለሙያዎች እየተሰጠ ያለውን የጤና አጠባበቅ ምክርና ትምህረት እንዲሁም በፍትህ መንፈሳዊ እንደተደነገገው ቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት በማድረግ ወረርሽኑን ማስቆም እንዲቻል በመላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጣም በተወሰኑ ካህናት መንፈሳዊ አገልግሎቱ እንዲሰጥ ሌሎች ካህናትና ምእመናን ለጊዜው በየቤታቸው በጸሎት እንዲወሰኑ፣ በአገልግሎት ላይ ለሚገኙ አገልጋይ ካህናትም በቤተ ክርስቲያኑ ቅጽረ ግቢ እንዲወሰኑ ሆኖ አስፈላጊው ሠርከ ህብስት የምግብ አቅርቦት እንዲዘጋጅላቸው እንዲደረግ፣

እግዚአብሔር አምላካችን የሕዝቡን ሁሉ ምሕላና ጸሎት፣ የካህናቱን አስተበቊኦት በርኀራኄው ሰምቶ፣ በቅዱሳኑ ቃልኪዳን፣ በወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም አማላጅነት ቁጣውን በምሕረቱ መዓቱን በትግዕስቱ አሳልፎ ፍጹም ደህንነትን እንደሚሰጠን እያመንን ፡-

2. በአሁኑ ጊዜ የወረርሽኙን ፍጥነት ለመቀነስ የሚደረገው ጥረት እንዳለ ሆኖ በቀጣይ በበሽታው እየተያዙ ለሚመጡ ወገኖቻችን ማቆያ ቦታ ማዘጋጀቱ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በመሆኑም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥር ከአዲስ አበባ ጀምሮ በመላው አህጉረ ስብከት የሚገኙ፡-
ሀ. መንፈሳዊ ኮሌጆች
ለ. የካህናት ማሠልጠኛዎች
ሐ. ዘመናውያን ት/ቤቶች አስፈላጊው ዝግጅት እንዲደረግላቸውና መሟላት የሚገባቸው ሁሉ ተሟልቶ ለሕሙማን ማቆያ እንዲውሉ ለማድረግ ወረርሽኙ እስከሚያበቃ ድረስ አገልግሎት መስጫ እንዲሆኑ የሚመለከተው አካል ተረክቦ እንዲያስተናግድባቸው ተወስኗል፡፡

3. በአሁኑ ጊዜ በወረርሽኙ ምክንያት መንግሥት ሕሙማንና የተቸገሩ አካላትን ለመርዳት እያደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ ከመንበረ ፓትርያርክ ለጊዜው ብር 3,000,000.00 (ሦስት ሚሊየን ብር) በመንግሥት ደረጃ ለተቋቋመው ርዳታ አሰባሳቢ በቤተ ክርስቲያናችን ስም እንዲሰጥ፣

4. በቤተ ክርስቲያናችን ሥር ለሚገኙ የሕጻናትና ማሳደጊያ ቦታዎች የሚገኙ ሕጻናትን እና ችግረኞችን በምግብና በንጽሕና መጠበቂያ መደጐም የሚያስፈልግበት ጊዜ በመሆኑ አስፈላጊው ርዳታ የማሰባሰብ ሥራ እንዲሠራና እንዲረዱ በቤተ ክርስቲያናችን ሥር በተቋቋመው ተስፋ ግብረ ኃይል በኩል የማስተባበሩ ሥራ እንዲሠራ፣

5. ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አሁን የያዝነውን የጾምና የጸሎት ጊዜ ምክንያት በማድረግ በቤተ ክርስቲያን ጸሎተ ቅዳሴውን በመምራትና በመባረክ መቆየታቸውን ቋሚ ሲኖዶስ ተገንዝቧል፡፡ ይሁን እንጂ በአሁኑ ጊዜ በአገራችን ያለው ወረርሽኝ በእጅጉ እየተስፋፋ በመሆኑና የተለየ አባታዊ ጸሎትና ሱባኤ የሚያስፈልግ ሆኖ በመገኘቱ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ከዛሬ መጋቢት 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ለዓለም ሰላምና ለሕዝቦች ደህንነት ሲባል ለጊዜው ለብቻቸው በልዩ የጾምና የጸሎት የሱባኤ ጊዜ እንዲቆዩ ቋሚ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ዓለማችንንና አገራችን ኢትዮጵያን ይጠብቅልን
ለሕዝባችንም ምሕረትንና ፈውስን ይስጥልን !
አሜን !

                       ምንጭ ከEOTC TV የተወሰደ

                         EOTC-DICAC/facebook

‹ Back to List