የዓለም አቀፍ የመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ጉባኤ በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ መከናወኑን አስመልክቶ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በእስክንድርያ የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የእንግሊዝ ሀገር ጳጳስ አቡነ አንጌሎስ ከብፁዕ አቡነ ሳሙኤል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቃ ጳጳሳት ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡

 

ማክሰኞ ሰኔ 2 ቀን 2007 ዓ/ም በልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በተደረገው በውይይቱ ወቅት ብፁዕ አቡነ አንጌሎስ በሚኖሩበት በእንግሊዝ ሀገር ከሠላሳ በላይ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት እንዳሏቸው

በእንግሊዝ ሀገር ያሉ ሌሎች ክርስቲያኖችንም በማስተባበር በዓለም አቀፍ ግንኙነቶች እና ውይይቶች ዙሪያ እንደሚሠሩ እንዲሁም ተስፋ የተባለ የበጎ አድራጎት ድርጅት እንዳላቸው ገልጸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በምታከናውናቸው የልማትና የበጎ አድራጎት ሥራዎች የበኩላቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡

 

ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል በበኩላቸውም ብፁዕነታቸው ባደረጉት ጉብኝትና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልማትና ክርስቲያናዊ ተራዶኦ ኮሚሽን እንቅስቃሴን በበኩላቸው ለመደገፍ ላሳዩት ልባዊ ፍላጎት የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ ብፁዕነታቸው ባቀረቡት ሐሳብ መነሻነት ወደፊት በልዩ ልዩ የልማት እንቅስቃሴዎች በትብብር ለመሥራት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡

Contact Us

Tel. +251111553566/ +251111563033
Fax: +251111551455
P.O. Box: 503 Addis Ababa, Ethiopia
E-mail: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it., This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
Web site: www.eotcdicac.org