በአሁኑ ጊዜ በመላው ዓለም በሚታየው ሕገ ወጥ የሠዎች ዝውውር እና ተያያዥ ጉዳዮች በርካታ ሰዎች ያልተጠበቀ አደጋ እየደረሰባቸው ይገኛል፡፡ በቅርቡ እንኳን አይ ኤስ ወይም አይ ኤስ አይ ኤስ እያለ ራሱን የሚጠራው አሸባሪ ቡድን በሜዲትራንያን በረሀ ጠረፍ ከሚገኙት ሀገሮች ውስጥ በሊቢያ በስደት በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ ክርስቲያን በመሆናቸው ብቻ ያደረሰው አሰቃቂ ወንጀል ልዩ ማሳያ ነው፡፡ ከዚህ ሰው ሰራሽ ከሆኑ በርካታ ችግሮች በተጨማሪ ተፈጥሯዊ በሆኑ በባህር ስጥመት፣ በልዩ ልዩ ከአየር ለውጥ ጋር በተያያዙ በሽታዎች፣ እና እንግልቶች በርካታ ዜጎች ለከፋ አደራ እየተጋለጡ ይገኛሉ፡፡

በዚህ ሰዎች የተሻለ የኑሮ ዕድል እና ስኬት ይገጥመናል በማለት ሰዎች ከቦታ ወደ ቦታ የመዘዋወር መብታቸውን በመጠቀም በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ደካማ ጎናቸውን በመጠቀም ላልተጠበቀ ኪሳራና የሕወት አደጋ እንዲጋለጡ የሚያደርጓቸው ሕገ ወጥ ደላላሎችና የሰዎች አዘዋዋሪዎችም እየተበራከቱና ራሱን የቻለ የገቢ ምንጭ አድርገው መውሰዳቸው ችግሩን የከፋና ዓለም አቀፍ ትኩረትን የሳበ እንዲሆን አድርጎታል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሰ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስም የችግሩን አስከፊነትና በዜጎቻችን ላይ እንዲሁም በመላው የሰው ልጅ ክቡር ሕይወት ላይ እየተፈጸመ ያለውን አሰቃቂ ተግባር ለማስቆም፣ ተጠቂዎችን ለመታደግ፣ የሰው ልጅ ሰብዓዊ ክብር በሁሉም ዘንድ እንዲከበር ዓለም ቀአፍ ጥሪን አስተላልፏል፡፡ በዚህ አሰቃቂ ድርጊት ላይ ያለምንም ሰብዓዊ ርኅራኄ ለራሳቸው ሥጋዊ ጥቅም የሚሯሯጡ ግለሰቦችንና ቡድኖችንም ተግባር በይፋ አውግዟል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ ከውገዘት በተጨማሪ ኢሰብኣዊ ድርጊትን ከመቃወም ባሻገር ትርጉም ያለው ለውጥና ዘላቂ መፍትሔ እንዲገኝም ከዓለም አቀፍ ተቋማትና ከሀገራች መንግሥት ጋር እየተመካከረ እንዲሠራ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ልማትና ክርሰቲያናዊ ተራዶኦ ኮሚሽን ኃላፊነቱን ሰጥቷል፡፡

ከሚያዝያ ፳፯ – ፴ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. በተካሔደው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ከመንግሥትና ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በቅርበት የሚሠራ ኮሚቴ በአስቸኳይ እንዲቋቋም ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

የልማት እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽንም ኮሚቴውን በማዋቀርና በኮሚሽኑ ሥር በሚገኘው የስደተኞችና ተመላሾች ድጋፍ መምሪያ አማካኝነት ርዳታ ሰጪዎችን በማስተባበር፣ በጉዳዩ ላይ ክትትል በማድረግ ሰፊ ሥራ እንዲሠራ መመሪያን አስተላልፏል፡፡ በቅርቡም “Response to Migrant Crisis” በሚል ርዕስ ጥሪ ማስተላላፉ ይታወሳል፡፡ ኮሚሽኑ ባስተላለፈው ጥሪ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ እና በአፍሪቃ በከፍተኛ ሥቃይ፣ እንግልትና አደጋ ውስጥ የሚገኙ ስደተኞች  ወገኖቻችንን ማኅበራዊና ሥነ ልቡናዊ፣ የጤናና የመልሶ መቋቋም ድጋፎችን ለማሟላት አስቸኳይ የርዳታና ድጋፍ ጥሪ አስተላልፏል፡፡ የጥሪው አጠቃላይ የድጋፍና የመልሶ ማቋቋም አቅጣጫዎችም በሦስት የተከፈሉ ሲሆኑ ኮሚሽኑ ቀደም ሲል በስደተኞችና ከስደት ተመላሾች መምሪያ ከሶማሌ፣ ለደቡብ ሱዳን፣ ከኤርትራና ከሌሎች የአፍሪካ አካባቢዎች ተሰደው ወደ በሀገራችን የተጠለሉ ስደተኞችን በመንከባከብ ከሚያደርጋቸው አንቅስቃሴዎች ጋር አብሮ የሚራመዱ መርሐ ግብሮች እንደሚሆኑም የኮሚሽኑ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ገልጸዋል፡፡ አሁን የሚካሔደው የድጋፍና የትብብር እንቅስቃሴ ሦስት አቅጣጫዎች (1ኛ) በስደት ያሉትን ወደ አገራቸው የመመለስ፣ (2ኛ) ከስደት ተመላሾች በኑሯቸው መልሶ ማቋቋም እና ወደ ቤተሰዎቻቸው መቀላቀል እና (3ኛ) የምክር አገልግሎት እና ሥነ ልቡናዊ ድጋፍ መስጠት ናቸው፡፡ በዚህ ረገድ ቤተ ክርስቲያኒቱ የሚጠበቅባትን ለማከናወን ከውጭ ሀገር ብቻ ሳይሆን ከሀገር ውስጥ ተቋማትም ድጋፍ ሊደረግ እንዲጠየቅና እና ሥራውን ብትብብር እንዲሠራ እንደሚገባም የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶ/ር አግደው ረዴ አስታውቀዋል፡፡

በገንዘብ የሚያደርጉ በጎ አድራጎቶችን በሚከተለው የኮሚሽኑ አድራሻ መጠቀም ይቻላል፤

COMMERCIAL BANK OF ETHIOPIA- Selassie Branch
ACCOUNT No. 1000010883214
SWIFT CODE; CBETETAA
P.O.BOX215
TEL.251-115-515 004
FAX. 251-115-511445/22
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
ADDIS ABABA/ETHIOPIA

ለበለጠ መረጃ ደግሞ የሚከተሉትን አድራሻዎች መጠቀም ይቻላል

EOTC DICAC
P.O.BOX 503
Addis Ababa/ETHIOPIA
TEL. 251-111-553 566/251-111-563 033
FAX. 251-111-551 455
e-mail This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
Web site: http://www.eotcdicac.org

 

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርቲያን

ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን

ፖ/ሣ/ቁጥር 503

ስልክ፡ 251-111-553 566/251-111-563 033
ፋክስ 251-111-551 455
ኢ-ሚይል This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
ድረ ገጽ: http://www.eotcdicac.org

Contact Us

Tel. +251111553566/ +251111563033
Fax: +251111551455
P.O. Box: 503 Addis Ababa, Ethiopia
E-mail: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it., This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
Web site: www.eotcdicac.org