የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ድጋፍ ዙሪያ ከአራት ዐሥርት ዓመታት በላይ ሲሠራ ቆይቷል፡፡ በዚህ የረጅም ጊዜ ሥራው ውስጥ ከዓለም አቀፍና ከሀገር ተቋማትና ከሀገራችን መንግሥት ጋር በትብብር በመሥራት ውጤታማ ተግባራትን አከናውኗል አሁንም እያከናወነ ይገኛል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በተለይ ሕገወጥ በሆነ መንገድ ከሀገራቸው ወጥተው ለከፋ አደጋ እየተጋለጡ ባሉ ኢትዮጵያውንና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ያለውን አስከፊ ገጽታ ለመቀየር የበኩሉን ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በቅርቡ መቀመጫው አዲስ አበባ በሆነው የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ተወካዮች ጋር በተመሳሳይ ርዕሰ ጉዳዮች በጋራ መሥራት ስለሚቻልበት ሁኔታ ውይይት አድርጓል፡፡ በውይይቱ ወቅት የኮሚሽኑ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልና ኮሚሽነር ዶ/ር አግደው ረዴ እንዲሁም የኮሚሽኑ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ አቶ ይልቃል ሽፈራው የተገኙ ሲሆን በጋራ መሠራት ስለሚገባቸው ጉዳዮች ሰፊ ውይይት አድረገዋል፡:

ውይይቱ የተጀመረው መ/ር አስቻለው ካሴ ባደረጉት ማስተዋወቅ ሲሆን የኮሚሽኑ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የስደተኞች ጉዳይ በአሁኑ ጊዜ ዓለም አቀፍ ትኩረት ያገኘ፣ አሳሳቢነቱ ከመቸውም ጊዜ የበለጠ እንደሆነና በተናጠል ሳይሆን በጋራ በመሆን መፍትሔ ልንሰጠው ይገባል በማለት ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡ ብፁዕነታቸው በተለይ በአሁኑ ጊዜ በሰው ላይ ይደርሳል ተብሎ የማይገመት መከራ በስደተኞች ላይ እየደረሰ መሆኑ ለችግሩ ልዩ ትኩረት እንድንሰጥ አድርጎናል ብለዋል፡፡ ከብፁዕነታቸው በመቀጠል ንግግር ያደረጉት አቶ ይልቃል ሽፈራው የኮሚሽኑ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ሲሆኑ በመምሪያ በአሁኑ ጊዜ እየተሠሩ ስላሉ አበይት ሥራዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶ/ር አግደው ረዴ በበኩላቸው ስበሰባው እጅግ ትልቅ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑንና በማመልከት ይኽን ዓለም አቀፍ ትኩረት ያገኘ ጉዳይ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጋር መሥራት ያለውን ጠቀሜታ እና ውጤታማ ሊሆን እንደሚችል በመገመት ወደ ልማትና ክርስቲያናዊ ተራዶኦ ኮሚሽን መምጣችሁ አግባብ ያለው ነው በማለት የአይኦኤም ተወካዮችን አመስግነዋል፡፡ በተለይ ቤተክርስቲያኒቱ ባላት መዋቅርና ተሰሚነት ሰብዓዊ አገልግሎት ያለምንም ልዩነት ለመስጠት፣ የመሠረታዊ ልማቶችን ለማሳካት፣ የኅብረተሰብን ተሳትፎ መሠረት ያደረገ የልማት እንቅቃሴ በማድረግና፣ ማኅበራዊ ግንኙነቶችን ለማጠናከር እየሠራች ያለውን የልማት እንቅስቃሴ ጋር በማጣመር ዜጎች ከስደት በፊት በሀገራቸው ለመለወጥ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ መደገፍ የሚቻልበት ሁኔታ ማመቻቸት እንዲሚገባ አሳስበዋል፡፡

የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ተወካይ የሆኑት ወ/ሮ ልዩነት ደምሳሽ የችግሩን አሳሳቢነት ድርጅቱ ካለው እንቅስቃሴና መረጃ በመነሣት ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፤ በየቀኑ እጅግ ብዙ ስደተኞችንና ከስደት ተመላሾችን እንደሚቀበሉ፣ በትንሽ የሠረተኞች ቁጥር በአሁኑ ጊዜ ሊቋቋት ከማይችሉበት ደረጃ መድረሳቸው፣ ከዚህም በተጨማሪ ሰፊ የሆነ የመረጃና የግንኙነት ክፍተት እንዳለ ያስረዱ ሲሆን ፤ በተለይ ቀደም ሲል በመግቢያው ላይ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ያቀረቡት ተባብሮ የመሥራት ሐሳብ ብቸኛ አማራጭ መሆኑን አበክረው ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም በተለይ በመረጃ ክፍተት የተነሣ ከሀገራቸው የሚሰደዱ ዜጎች ለሕገ ወጥ ደላሎችና የሰዎች አዘዋዋሪዎች እንዲጋለጡ እንዳደረጋቸው ገልጸዋል፡፡ የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ተወካይ ከሆኑት ውስጥ አብረው በስብሰባው የተገኙት ወ/ሮ ሜሮን በተጨማሪ እንደገለጹት በስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ዙሪያ፣ በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ በሕገወጥ ደላሎች እና ተያያዝ ጉዳዮች ሥልጠናና በተከታታይ ሕዝብን የማሳወቅ ሥራ ሊሠራ እንደሚገባ በመግለጽ የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በዚህ ረገድ ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚችል አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻ የኮሚሽኑ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል በመስኩ ከቤተ ክርስቲያኒቱ የልማትና ክርስቲያናዊ ኮሚሽን ጋር አብሮ በሚሠራበት ጉዳይ ተከታታይ ውይይት እንዲደረግ ማሳሰቢያ በመስጠት ስብሰባው ተጠናቋል፡፡

ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ከአይ/ኦ/ኤም ልዑካን ጋር በስደተኛችና ከስደት ተመላሾች ዙሪያ ውይይት አደረገ

የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ድጋፍ ዙሪያ ከአራት ዐሥርት ዓመታት በላይ ሲሠራ ቆይቷል፡፡ በዚህ የረጅም ጊዜ ሥራው ውስጥ ከዓለም አቀፍና ከሀገር ተቋማትና ከሀገራችን መንግሥት ጋር በትብብር በመሥራት ውጤታማ ተግባራትን አከናውኗል አሁንም እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በተለይ ሕገወጥ በሆነ መንገድ ከሀገራቸው ወጥተው ለከፋ አደጋ እየተጋለጡ ባሉ ኢትዮጵያውንና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ያለውን አስከፊ ገጽታ ለመቀየር የበኩሉን ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በቅርቡ መቀመጫው አዲስ አበባ በሆነው የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ተወካዮች ጋር በተመሳሳይ ርዕሰ ጉዳዮች በጋራ መሥራት ስለሚቻልበት ሁኔታ ውይይት አድርጓል፡፡ በውይይቱ ወቅት የኮሚሽኑ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልና ኮሚሽነር ዶ/ር አግደው ረዴ እንዲሁም የኮሚሽኑ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ አቶ ይልቃል ሽፈራው የተገኙ ሲሆን በጋራ መሠራት ስለሚገባቸው ጉዳዮች ሰፊ ውይይት አድረገዋል፡:

ውይይቱ የተጀመረው መ/ር አስቻለው ካሴ ባደረጉት ማስተዋወቅ ሲሆን የኮሚሽኑ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የስደተኞች ጉዳይ በአሁኑ ጊዜ ዓለም አቀፍ ትኩረት ያገኘ፣ አሳሳቢነቱ ከመቸውም ጊዜ የበለጠ እንደሆነና በተናጠል ሳይሆን በጋራ በመሆን መፍትሔ ልንሰጠው ይገባል በማለት ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡ ብፁዕነታቸው በተለይ በአሁኑ ጊዜ በሰው ላይ ይደርሳል ተብሎ የማይገመት መከራ በስደተኞች ላይ እየደረሰ መሆኑ ለችግሩ ልዩ ትኩረት እንድንሰጥ አድርጎናል ብለዋል፡፡ ከብፁዕነታቸው በመቀጠል ንግግር ያደረጉት አቶ ይልቃል ሽፈራው የኮሚሽኑ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ሲሆኑ በመምሪያ በአሁኑ ጊዜ እየተሠሩ ስላሉ አበይት ሥራዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶ/ር አግደው ረዴ በበኩላቸው ስበሰባው እጅግ ትልቅ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑንና በማመልከት ይኽን ዓለም አቀፍ ትኩረት ያገኘ ጉዳይ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጋር መሥራት ያለውን ጠቀሜታ እና ውጤታማ ሊሆን እንደሚችል በመገመት ወደ ልማትና ክርስቲያናዊ ተራዶኦ ኮሚሽን መምጣችሁ አግባብ ያለው ነው በማለት የአይኦኤም ተወካዮችን አመስግነዋል፡፡ በተለይ ቤተክርስቲያኒቱ ባላት መዋቅርና ተሰሚነት ሰብዓዊ አገልግሎት ያለምንም ልዩነት ለመስጠት፣ የመሠረታዊ ልማቶችን ለማሳካት፣ የኅብረተሰብን ተሳትፎ መሠረት ያደረገ የልማት እንቅቃሴ በማድረግና፣ ማኅበራዊ ግንኙነቶችን ለማጠናከር እየሠራች ያለውን የልማት እንቅስቃሴ ጋር በማጣመር ዜጎች ከስደት በፊት በሀገራቸው ለመለወጥ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ መደገፍ የሚቻልበት ሁኔታ ማመቻቸት እንዲሚገባ አሳስበዋል፡፡

የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ተወካይ የሆኑት ወ/ሮ ልዩነት ደምሳሽ የችግሩን አሳሳቢነት ድርጅቱ ካለው እንቅስቃሴና መረጃ በመነሣት ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፤ በየቀኑ እጅግ ብዙ ስደተኞችንና ከስደት ተመላሾችን እንደሚቀበሉ፣ በትንሽ የሠረተኞች ቁጥር በአሁኑ ጊዜ ሊቋቋት ከማይችሉበት ደረጃ መድረሳቸው፣ ከዚህም በተጨማሪ ሰፊ የሆነ የመረጃና የግንኙነት ክፍተት እንዳለ ያስረዱ ሲሆን ፤ በተለይ ቀደም ሲል በመግቢያው ላይ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ያቀረቡት ተባብሮ የመሥራት ሐሳብ ብቸኛ አማራጭ መሆኑን አበክረው ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም በተለይ በመረጃ ክፍተት የተነሣ ከሀገራቸው የሚሰደዱ ዜጎች ለሕገ ወጥ ደላሎችና የሰዎች አዘዋዋሪዎች እንዲጋለጡ እንዳደረጋቸው ገልጸዋል፡፡ የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ተወካይ ከሆኑት ውስጥ አብረው በስብሰባው የተገኙት ወ/ሮ ሜሮን በተጨማሪ እንደገለጹት በስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ዙሪያ፣ በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ በሕገወጥ ደላሎች እና ተያያዝ ጉዳዮች ሥልጠናና በተከታታይ ሕዝብን የማሳወቅ ሥራ ሊሠራ እንደሚገባ በመግለጽ የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በዚህ ረገድ ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚችል አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻ የኮሚሽኑ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል በመስኩ ከቤተ ክርስቲያኒቱ የልማትና ክርስቲያናዊ ኮሚሽን ጋር አብሮ በሚሠራበት ጉዳይ ተከታታይ ውይይት እንዲደረግ ማሳሰቢያ በመስጠት ስብሰባው ተጠናቋል፡፡

Contact Us

Tel. +251111553566/ +251111563033
Fax: +251111551455
P.O. Box: 503 Addis Ababa, Ethiopia
E-mail: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it., This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
Web site: www.eotcdicac.org