ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ጋር በመሆን ከሰኔ 26-27 ቀን 2007 ዓ.ም ወደ ትግራይ ክልል ሐዋርያዊ ጉዞ በማድረግ ከጎበኟቸው ቅዱሳት መካናት አንዱ እሑድ ሰኔ 28 ቀን 2007 ዓ.ም የጎበኙት የጪኽ መካነ ሕይወት ቅድስት ሥላሴ ገዳም ይገኝበታል፡፡

በትግራይ ክልል በተንቤን ወረዳ የሚገኘው የጪኽ መካነ ሕይወት ቅድስት ሥላሴ ገዳም ቅዱስ ፓትርያርኩ ከሕፃንነታቸው ጀምሮ ያደጉበትን፣ ተምረው ያስተማሩበትንና ሥርዓተ ምንኩስና የፈጸሙበት ታሪካዊ ገዳም ነው፡፡

 

 

 

 

በጨኽ ገዳም የሚገኘው የኪዳነ ምሕረት ከፊል ፍልፍል ዋሻ ቤተ ክርስቲያን

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ከጪኽ መካነ ሕይወት ቅድስት ሥላሴን ገዳም ከወጡ ከ50 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የጎበኙት መሆኑን የገለጹ ሲሆን አሁን የገዳሙ አበምኔት የሆኑት መምህር ነአኵቶ ለአብ በልጅነት እንደሚያቋቸው ተናግረዋል፡፡ ቅዱስነታቸው በጪኽ መካነ ሕይወት ቅድስት ሥላሴ ገዳም እንደደረሱ በርካታ መነኰሳት፣ የአካባቢው ምዕመናን፣ የሰንበት ትምሀርት ቤት ወጣቶች ደማቅ አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራዶኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል፣ ኮሚሽነር ዶ/ር አግደው ረዴና የኮሚሽኑ ልዩ ልዩ መምሪያዎች ኃላፊዎች በቦታው ተገኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት በገዳሙ አውደ ምህረት ከተካሄዱት መርሐ ግብሮች ባሻገር ቅዱስነታቸው ቀደም ሲል ለገዳሙ ድጋፍ እንዲሆኑ በልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ከተሠሩ ሥራዎች መካከል የውሃ ሥራዎችን ተመልክተዋል፡፡

 

በልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን የተሠሩ የውሃ ሥራዎች 

Contact Us

Tel. +251111553566/ +251111563033
Fax: +251111551455
P.O. Box: 503 Addis Ababa, Ethiopia
E-mail: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it., This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
Web site: www.eotcdicac.org