ሕገ ወጥ ስደትን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መልዕክት

የሰዎች ዝውውር በአግባቡ ማለትም ህጋዊውን መንገድ ከተከተለና መብትና ግዴታችንን በምናውቅበት መንገድ ሲካሄድ ለተዘዋወረው (ለተጓዡ ) ለላኪ እና መዳረሻ ሀገሮች እንዲሁም ለቤተሰብና ለአጠቃላይ ማኀበረሰቡ ሰፊ ጠቀሜታ አለው፡፡ ህጋዊ መንገድን የተከተለ የሰዎች ዝውውር የሥራ የትምህርት፣ የዕውቀት፣ የልምድ፣ የቴክኖሎጂ ፣ የባህል ልውውጥን የሚያመቻቹ እድሎችን ይፈጥራል፡፡በ2013 በዓለማችን የሰዎች ዝውውር ቁጥር 232 ሚሊዮን እንደደረሰ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ ይህ ቁጥር በ2000 እ.አ.አ 175 ሚሊዮን፣ በ1990

በ"አደራ በጎ አድራጎት ድጎማ' እና በ"በጎ ፈቃደኝነት' ረቂቅ መመሪያዎች ላይ የተሳካ ውይይት ተካሄደ

በቅርቡ የወጡ አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በዓለማችን ላይ የወላጅ አጥ ሕጻናት ቁጥር ከ16 ሚሊዮን በላይ ሲሆን በሀገራችን ደግሞ ወደ 900 ሺህ ገደማ እንደሚደርስ ይገመታል። እ.ኤ.አ በ2013 ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ ሰዎች ቁጥር ከ769 ሺህ በላይ እንደሆነ ይታሰባል፡፡ በሌላም በኩል በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ፀረ-ኤች.አይ.ቪ መድኃኒት የሚያስፈልጋቸው ሕሙማን ቁጥር ከ500,000 በላይ ይገመታል፡

"በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ"

"ነገር ግን ወንድሞች ሆይ፥ ተስፋ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች ደግሞ እንዳታዝኑ አንቀላፍተው ስላሉቱ ታውቁ ዘንድ እንወዳለን። ኢየሱስ እንደ ሞተና እንደ ተነሣ ካመንን፥ እንዲሁም በኢየሱስ ያንቀላፉቱን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ያመጣቸዋልና። ... በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፡፡" (1 ተሰ 4፡13-16)

የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በስደተኛችና ከስደተ ተመላሾች ጉዳይ የአቋም መግለጫ አወጣ

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጣር ከጁን 07 እስከ 12 ቀን 2015 ዓ/ም በአርሜንያ ኤችሚሀድዘን እተካሄደ ባለው የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ በጁን 12 ቀን 2015 ዓ/ም በስደተኛችና ከስደተ ተመላሾች ጉዳይ የአቋም መግለጫ አውጥቷል፡፡ በዚሁ መግለጫ በተለይ በብዙ ስቃይና አስጊ ሁኔታዎች ላይ ከአንዱ ዓለም ክፍል ወደ ሌላው ዓለም ክፍል ለሚጓዙ ስደተኞችን ደኅንነት በተመለከተ ያለምንም ቅድመ ሁኔታና ልዩነት መላው የዓለም መንግሥታትና የኅብረተሰብ ክፍሎች የሥነ ልቦናና የሕግ ግዴታ እንዳለባቸው አሳስቧል፡፡

በዚሁ መግለጫ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ቁጥራቸው እጅግ ብዙ የሆነ ስደተኛች በሜዲትራንያን ባሕር፣ በባንግላዲሽ፣ እና በሌሎች የዓለም ክፍሎ የደረሰባቸውን የሞት አደጋ በማውሳት እንዲሁም በቅርቡ ራሱን አይ ኤስ እያ በሚጠራው አሸባሪ ቡድን በሊቢያ የተገደሉትን ኢትዮጵያውን፣ በደቡብ አፍሪካ ዜኖፎቢያ በስደተኞች ላይ የደረሰውን ከፍተኛ የንብረትና የሕይወት አደጋ አውግዟል፡፡

ሙሉውን ለማንበብhttp://www.oikoumene.org/en/press-centre/news/wcc-executive-committee-speaks-out-on-migrant-crises

የልማት መምሪያ ከፊንላንድ የፊንአንትሮፒያ እና የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ተወካዮች ጋር የመስክ ጉብኝት አደረገ

የልማትና ክርስቲያናዊ ተራዶኦ ኮሚሽን የልማት መምሪያ ከሚያከናውናቸው የልማት ሥራ መርሐ ግብሮች ውስጥ አንዱ በሆነውና በሐይቅ የተቀናጀ ልማት መርሐ ግብር Haik Integrated Rural Development Project (IRDP)  እ/እ/አ ከፊብሩዋሪ 28 ቀን 2015 ቀን እስከ ማርች 06 ቀን 2015 ድረስ የመስክ ጉብኘትት ተደረገ፡፡ የመስክ ጉብኝቱ የተከናወን የለጋሽ ድርጅት የሆነው የፊን ላንድ ፊልአንትሮፒያ ተወካዮች የሆኑት ሚስ ሪና ነጉያን የፊልአንትፒያ ዳይሬክተር፣ እና ሚ/ስ ኤማ ፖሲ የፊልአንትሮፒያ ቦርድ አባል የተገኙ ሲሆን በፊን ላንድ መንግሥት የፊልአንትፒያ ድርጅቶች ከሀገራቸው ውጭ የሚሠሩትን የበጎ አድራጎት ሥራ ክትትል የሚያደርገው የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተወካዮች ሚ/ስ ሊና እና ሚ/ስ ሌላ በመስክ ጉብኝቱ አብረው የተጓዙት ናቸው፡፡

ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን የደቡብ ሱዳን አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ በደቡብ ሱዳን ሰላም ጉዳይ ያደረጉትን ስብሰባ አስተናገደ

 

በደቡብ ሱዳን የተከሰተውን የርስ በርስ ግጭት አስመልክቶ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ጋር በመተባበር መፍትሔ ለማፈላላግ ከሚያዝያ 6-7 ቀን 2007 ዓ/ም ድረስ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ቅዱስ ሲኖዶስ መሰብሰቢያ አዳራሽ ስብሰባ ተደርጓል፡፡

 

Contact Us

Tel. +251111553566/ +251111563033
Fax: +251111551455
P.O. Box: 503 Addis Ababa, Ethiopia
E-mail: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it., This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
Web site: www.eotcdicac.org