ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን የኤች አይቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ መምሪያ በልማት ወንጌል መርሐ ግብር ላይ የአሠልጣኞች ሥልጠና አካሄደ

በልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን የኤች አይቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ መምሪያ ከሚካሄዱት መርሐግብች አንዱና ዋናው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የኤች አይቪ ኤድስን ጨምሮ በልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ጤና ጉዳዮች ያላትን አስተምህሮ የምትገልጽበት የልማት ወንጌል የተባለው መርሐ ግብር ነው፡፡ መርሐ ግብሩ የሚያተኩረው በቅድስት ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ ሊቃውንት ጉባኤ አባላት የተዘጋጀው የልማት ወንጌል መጽሐፍን ማስፈጸም ሲሆን ለዚሁ እንዲረዳ ከየአህጉረ ስብከቱ የተውጣጡ ካህናትንና ሰባክያነ ወንጌልን ማሠልጠን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ይህ ሥልጠና መዘጋጀቱን የሥልጠናው አስተባባሪዎች ገልጸዋል፡፡

ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ከአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አክሲዮን ማኅበር ጋር የጋራ ስምነት ተፈራረመ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልማትና ክርስቲያናዊ ተራዶኦ ኮሚሽን በኢትዮጵያ  ቀደምት ከሚባሉት የተራድኦ ድርጅቶች አንዱ ሲሆን በሀገሪቱ መንግሥታዊ ያልሆነ ግንባር ቀደም የልማት አጋር ድርጅት ነው፡፡ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ላለፉት አርባ ዓመታት በልዩ ልዩ የልማት ዘርፎች በተለይ በገጠር ልማት፣ በንጹሕ ውሃ አቅርቦት፣ በግልና በአካባቢ ንጽሕና አጠባበቅ፣ በሰብአዊ ርዳታና መልሶ ማቋቋም፣ በተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ፣ በስደተኞችና ከስደት ተመላሾት ድጋፍ፣ በኤች አይቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጣር፣ ቤተ ክርስያንን ባማከለ የልማት ሥራ፣ በመሳሰሉት በርካታ የልማት ሥራዎች የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የተራድኦ ተልእኮ የሚያስፈጽም ተቋም ነው፡

የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ድጋፍ መምሪያ ሴፍ ሐውስ የተባለ መርሐ ግብር መጀመሩን አስታወቀ

የሰው ልጅ በልዩ ልዩ ተፈጥሮአዊና ሰው ሠራሽ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የመኖሪያ ቀየውን ለቆ ቅርብና ሩቅ ሀገሮች ይሰደደል፡፡ ይሁን እንጅ ስደት አንዱ አማራጭ ቢሆንም ሁል ጊዜ ምቹና ደኅንነቱ የተጠበቀ ላይሆን ይችላል፡፡ ሰዎች ከሀገራቸው ሲወጡ በቀላሉ ለማግኝት ከሚከብዷቸው ከትምሀርት፣ ከጤና፣ ከሙያ ሥልጠና ባሻገር በስደት ወቅት የሚያጋጥሙ ያልተጠበቁና ከአቅም በላይ የሆኑ አካላዊ፣ ሥነ ልቦናዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ደኅንነት የሚፈትኑ ችግሮች ይኖራሉ፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን የ2006 ዓ.ም የስራ አፈጻጸምና የ2007 እቅድ ሪፖርት

  1. የሪፖርቱ አላማ

የዚህ ሪፖርት ዋና አላማ የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በ2006 ዓ.ም የስራ ዘመን ያከናወናቸውን ተግባራት፣ ያጋጠሙ ችግሮችንና እንደዚሁም የ 2007 ዓ.ም እቅድን ለማቅረብ ነው፡፡

2. የሪፖርቱ ይዘት

ይህ ሪፖርት በየስራ ዘርፉ የተከናወኑ አበይት ተግባራትን፣ ስራዎችንም ለማከናወን የተመደበ በጀት፣ ከለጋሾች የተገኘ የገንዘብ መጠንና የወጣ ወጭን የሚገልጽና እንደዚሁም የ2007 ዓ.ም እቅድን ጠቅለል ባለ መልኩ ያካተተ ነው፡፡

እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ 2007 ዓ.ም በሰላምና በጤና አደረሳችሁ

ቸሩ ፈጣሪያችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን የዘመነ ኦሪት መጨረሻ፤የዘመነ ሐዲስ መነሻ ሆኖ ከሚታወቀውና ከሚታሰበው፤በአጥማቂነቱ ካህን፤የዓለምን ኃጢአት ይቅር የሚል ከእኔ በኋላ ይመጣል በማለቱ ነቢይ ስለ ክርስቶስ ሕይወቱን በመስጠቱ ሰማዕት ከሆነው ቅዱስ ዮሐንስ በዓል፣ የዘመን መለወጫ፤ ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ 2007 ዓ.ም በሰላም፤በጤና እና በሕይዎት አደረሳችሁ!!!!!

የሴቶችና የልጃገረዶችን ደኅንነት የሚያረጋግጥ ሞዴል ማዕከል ተከፈተ

መልካም ቤተሰብ የሚፈጠረው የሴቶችና የልጃገረዶች መብትና ደህንነት ሲጠበቅ ነው፡፡ ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ ድጋፍና ክብካቤ የተደረገላቸው ሴቶች ለወገናቸው ተቆርቋሪ፣ ለሀገራቸው አሳቢና ለእምነታቸው ቀናኢ የሆኑ ዜጎችን ለማፍራት ዋስትና የሚጣልባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ገለጸች፡፡

ልማት ኮሚሽኑ በሊቦ ከምከም ወረዳ ከ4796 በላይ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ እያደረገ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በደቡብ ጎንደር ዞን በሊቦ ከምከም ወረዳ ውስጥ በከፈተው የገጠር ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት አማካይነት ከ4796 በላይ አርሶ አደሮችን  የልማቱ ተጠቃሚ እያደረገ ነው፡፡ ፕሮጀክቱ የንጹሕ መጠጥ ውኃ፣ የተሻሻሉ በጎችን፣ፍየሎችን፣ምርጥ ዘሮችን በማቅረብ የአርሶ አደሮች ኑሮ እንዲሻሻል ከማድረጉም በላይ በባህላዊ መንገድ የመስኖ ውኃን በማባከን ይጠቀሙበት የነበረውን  በማስቀረት በዘመናዊ የመስኖ ውኃ አጠቃቀም አማካይነት ነዋሪዎች ምርታቸውን ማሳደግ እንዲችሉ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡

ሥልጠና እና ጾታዊ ጥቃት

በአንድ ወቅት አንድ ሰው ዛፍ በመቁረጥ ላይ እንዳለ አንድ ሌላ ሰው በድንገት ይደርስና ይመለከተዋል፡፡ ዛፍ የሚቆርጠው ሰው በፊቱ ላይ ከባድ የድካም ስሜት ይነበባል፡፡ ላቡም ከፊቱ ላይ ይንጠባጠባል፡፡ ይህንን ያስተዋለው መንገደኛም እንዲህ ሲል ዛፍ ቆራጩን ጠየቀው፡- ወንድሜ ሆይ! ይህን ዛፍ መቁረጥ ከጀመርክ ስንት ሰዓት ሆነህ? ቆራጩም አራት ሰዓት ብሎ መለሰለት፡፡ መንገደኛው ችግሩ የመጥረቢያው ደነዝነት መሆኑ ስለገባው ቆራጩን እንዲህ በማለት ይመክረዋል፡፡

Contact Us

Tel. +251111553566/ +251111563033
Fax: +251111551455
P.O. Box: 503 Addis Ababa, Ethiopia
E-mail: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it., This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
Web site: www.eotcdicac.org