ነስአ ደዌነ ወጾረ ሕማነ

ስለኛ ደዌአችንን ሕመማችንን ተሸከመ፡፡

የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ ነስአ ደዌነ ወጾረ ሕማመነ የእኛ ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንና ኃጢአታችንን ተሸከመ ስለ መተላለፋችን ሕጉንና ትእዛዙን በማፍረሳችን ስለ እኛ ቆሰለ፣ ስለ በደላችን ደቀቀ፣ ማለትም ሥጋውን ቆረሰ ደሙን አፈሰሰ በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደገነት ከውርደትና ከኃሳር ወደክብር ተመለስን፡፡ የዓለምን ሁሉ መድኃኒት የሁላችን ዕዳ፣ ፍዳና በደል በእርሱ ላይ አኖረ (ኢሳ 53፡4-5)

ቤተ-ክርስቲያኗ የሴቶችንና የልጃገረዶችን ጥቃት እየታደገች ነው

የኢትዮጵያ ኦርዶክስ ተዋሕዶ ቤተ- ክርስቲያን  የሴቶችንና የልጃ ገረዶችን ሕይወት የተቃና ለማድረግ እያበረከተች ያለው እንቅስቃሴ ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ፡፡  ይህንንም ተግባራዊ የምታደርገው በልማት ኮሚሽኑ ስር በሚገኘው በኤች አይቪ ኤድስ መከላከያና መቆጠጠሪያ መምሪያ  አማካይነት ነው፡፡

ልማት ኮሚሽኑ ዓመታዊ የምክክር ጉባኤ አካሔደ

የስብሰበው ተካፋዮች በከፊልየልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሕፃናትን በመንከባከብ፣ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን በመከላከል በተለይ ቫይረሱ ከነፍሰ-ጡር እናት ወደ ጽንሱ እንዳይተላለፍ የተደረጉት ጥረቶችና የተሰጡት ትምህርቶች ውጤታማ መሆናቸውን ለመገምገም እንዲቻል የምክክር ጉባኤ በሐዋሳ ከተማ ተካሄደ፡፡

ለጤናማ እናትነት፣ ለሥነ-ተዋልዶ ጤና እና ለጾታ እኩልነት የካህናት ሥልጠና በጭሮ ከተማ

የአካባቢው ስም ምዕራብ ሐረርጌ ይባላል፡፡ ቦታው በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከሚገኙት ዞኖች አንዱ ነው፡፡ ጭሮ የዞኑ ርእሰ ከተማ ስትሆን ከአዲስ አበባ በስተምሥራቅ 326 ኪሎ ሜትር ርቃ ትገኛለች፡፡ በዞኑ የተለያዩ ቋንቋዎች ያሉ ሲሆን ኦሮምኛ የሥራ ቋንቋ እና አብዛኛው ኅብረተሰብ የሚናገረው ቋንቋ ነው፡፡ በሀገረ ስበከቱ ውስጥ 26 አድባራት፣ 9 የወረዳ ቤተ-ክህነት ጽሕፈት ቤቶችና ሁለት ገዳማት ይገኛሉ፡፡

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከ350 በጎ አድራጊ ድርጅቶች መካከል ኤችይ ቪ ኤድስን በመከላከል ተግባር አሸናፊ ሆና ተሸለመች

የክርስቲያን ልማት እና በጎ አድራጊ ማኅበራት ኅብረት የተመሠረተበትን 40ኛ ዓመት በዓል ሲያከብር በየዓመቱ የሚያካሂደውን የላቀ የሥራ አፈጻጸም ያሳዩ አባላት የእውቅና እና የሽልማት ሥነ-ሥርዓት በያዝነው ወር የመጀመርያ ሳምንት ተካሒዷል፡፡ ሥነ ሥርዓቱ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን፣ አምስት ሚኒስትር ዲ.ኤታዎች እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የማኅበሩ የበላይ ኃላፊዎች እንዲሁም ለጋሽ ድርጅቶች በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል፡፡

 

ቤተ ክርስቲያኗ ሥነ ተዋልደን፤ ጤናማ እናትነትንና ሥርዓተ-ፆታን ለማስረጽ የጀመረችውን ተግባር እያጠናከረች ነው

የኢትዮጵያ አርቶዶከስ  ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች የሚወገዱበትን፣ የሴቶች ጥቃት የሚያከትምበትንና ሴቶች ከዘልማዳዊ የአኗኗር  ዘይቤ ተላቅቀው ከኩሻና ኑኖ ወጥተው፣ በትምህርት ተኮትኩተውና የራሳቸውን ኢኮኖሚ አዳብረው ከወንድ ጥገኝነት ነፃ ሚወጡበትን ስልት በመቀየሰ ለተግባረዊነቱ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ፡፡

እግዚያብሔር እግዚእ አስተሰርየ ለነ፤ጌታ እግዚያብሔር ተገለጠልን

እንደ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ የቤተክርስቲያናችን ሥርዓት ዛሬ ያለንበት ወቅት ዘመነ አስተርእዮ ይባላል፡፡ ይህም የመገለጥ ወራት ማለት ነው፡፡ እግዚያብሔር ወልድ ስለእኛ ስለ ሰዎች ስለ መዳናችን ሰው ሆኖ በሥጋ ተገልጦ መታየቱ የሚታሰብበት ወቅት ነው፡፡ በተለይም በዛሬው ዕለት የምናከብረው በዓለ ጥምቀት አስተርእዮ ተብሎ ይጠራል፡፡ ምክንያቱም በዚህ ዕለት ምሥጢረ ሥላሴ ተገልጧል፡፡

ልማት ኮሚሽኑ በ12.9 ሚሊዮን ብር በዘላቂ አካባቢና በግል ንጽሕና አጠባበቅ ዙሪያ በሦስት ከተሞች ላይ ለመሥራት የተፈራረመውን ፕሮጀክት ይፋ አደረገ

በኢትዮጵያ ሥር ነቀል የግልና የአካባቢ ንጽሕናን  ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት ለማጎልበት ከአውሮፓ ኅብረት በኔዘርላንድ የልማት ድርጅት በኩል በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የልማትና ክርስቲናዊ ተራድኦ ኮሚሽንና የኔዘርላንድ የልማት ድርጅት ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ጋር የአጋርነት ሰምምነት ይፋ ሆነ፡፡

Contact Us

Tel. +251111553566/ +251111563033
Fax: +251111551455
P.O. Box: 503 Addis Ababa, Ethiopia
E-mail: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it., This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
Web site: www.eotcdicac.org