መግለጫ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ የእናቶችና ሕፃናት ሥርዓተ ምግብ እንዲሻሻል የተዘጋጀውን የሥርዓተ ምግብ የስብከት መመሪያ መረቁ፡፡
ይህም ለነፍሰጡርና ለሚያጠቡ እናቶች ትኩረት በመስጠትና እናቶችና ከሁለት ዓመት በታች የሆኑ ሕጻናት በአጽዋማት ጊዜ ስለሚኖራቸው አመጋገብና ስለ ሥርዓተ - ምግብ ለማስተማር የተዘጋጀ ነው፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በጪኽ መካነ ሕይወት ቅድስት ሥላሴን ገዳም ጉብኝት አደረጉ፤

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ጋር በመሆን ከሰኔ 26-27 ቀን 2007 ዓ.ም ወደ ትግራይ ክልል ሐዋርያዊ ጉዞ በማድረግ ከጎበኟቸው ቅዱሳት መካናት አንዱ እሑድ ሰኔ 28 ቀን 2007 ዓ.ም የጎበኙት የጪኽ መካነ ሕይወት ቅድስት ሥላሴ ገዳም ይገኝበታል፡፡

ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ከአይ/ኦ/ኤም ልዑካን ጋር በስደተኛችና ከስደት ተመላሾች ዙሪያ ውይይት አደረገ

 

የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ድጋፍ ዙሪያ ከአራት ዐሥርት ዓመታት በላይ ሲሠራ ቆይቷል፡፡ በዚህ የረጅም ጊዜ ሥራው ውስጥ ከዓለም አቀፍና ከሀገር ተቋማትና ከሀገራችን መንግሥት ጋር በትብብር በመሥራት ውጤታማ ተግባራትን አከናውኗል አሁንም እያከናወነ ይገኛል፡፡

ኮሚሽኑን የሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ተጎጅዎችን አስመልክቶ ዓለም አቀፍ የድጋፍ ጥሪ አስተላለፈ

 

በአሁኑ ጊዜ በመላው ዓለም በሚታየው ሕገ ወጥ የሠዎች ዝውውር እና ተያያዥ ጉዳዮች በርካታ ሰዎች ያልተጠበቀ አደጋ እየደረሰባቸው ይገኛል፡፡ በቅርቡ እንኳን አይ ኤስ ወይም አይ ኤስ አይ ኤስ እያለ ራሱን የሚጠራው አሸባሪ ቡድን በሜዲትራንያን በረሀ ጠረፍ ከሚገኙት ሀገሮች ውስጥ በሊቢያ በስደት በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ ክርስቲያን በመሆናቸው ብቻ ያደረሰው አሰቃቂ ወንጀል ልዩ ማሳያ ነው፡፡

EOC-DICAC Achievements in Endamehoni Food Security Project

Challenging but possible

Hara traditional irrigation is found in Endamehoni wereda, southern zone of Tigray. The site is located in one of the steep valises in the region which is not convenient for development intervention, however, the project in collaboration with its stakeholders’ is able to plan and implement the challenging irrigation project in the area. The project aims to contribute towards o food security enhancement by constructing demonstrative irrigation infrastructure in the inconvenient and neglected area and support land less youths to get irrigable land in their locality.

ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የልማትና ክርስቲያናዊ ተራዶኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ በእስክንድርያ የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የእንግሊዝ ጳጳስ አቡነ አንጌሎስ ጋር ተገናኝተው ተወያዩ

የዓለም አቀፍ የመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ጉባኤ በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ መከናወኑን አስመልክቶ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በእስክንድርያ የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የእንግሊዝ ሀገር ጳጳስ አቡነ አንጌሎስ ከብፁዕ አቡነ ሳሙኤል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቃ ጳጳሳት ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡

Review meeting of HIV/AIDS Prevention & Control Department, focusing on Developmental Bible project

Developmental Bible project is one the seven projects in the HIV and AIDS Prevention & Control Department. The project in the 2014-2015 fiscal year which was started as of July 1, 2014 focuses on promoting dialogue among youth and mobilizing communities on issues related to sexual and reproductive health, HIV, gender-based violence and gender equality. During the last fiscal year the project has been implemented in nine Theological colleges & clergy training centers found in the six regions:

Contact Us

Tel. +251111553566/ +251111563033
Fax: +251111551455
P.O. Box: 503 Addis Ababa, Ethiopia
E-mail: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it., This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
Web site: www.eotcdicac.org