Skip to main content

  ኮቪድ 19 እና ግጭት ወቅታዊ የሰው ልጅ ፈተናዎች ABGELAUFEN SEIT 03.05.2020

  05.05.2020 Top news Media info
  ኮቪድ 19 እና ግጭት ወቅታዊ የሰው ልጅ ፈተናዎች

  ዓለም ከተፈጠረ ዘመን ከተቆጠረ የሰው ልጅ በዘመናት መካከል በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ አልፎል እያለፈም ይገኛል፡፡ ፈተናዎቹ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሠራሽ ሲኾኑ መልካቸውን እየቀያየሩ የሰው ልጅ ሕይወትን ዋጋ እያስከፈሉት ይገኛሉ፡፡

   

   

   

   

   

   

   

   

   

   

   

   

   

   

   

   

   

   

   

   

   

   

  Warimages-2 coronavirus-1

  የዛሬ ጽሑፌ የሚያተኩረው በተለያዩ ጊዚያት የሚነሡ ግጭቶች (ጦርነቶች) እና በዓለማችን የሚነዙ ቫይረሶች (ወረርሽኞች) በተለይም በዘመናችን ከተነሣው የኮረና (ኮቪድ 19) ቫይረስ ጋር ያላቸውን ተዛምዶ መመልከት ነው፡፡

  በዓለማችን በተለያዩ አገራት መካከል ታላላቅ ጦርነቶች ተደርገዋል፡፡ ከተደረጉት ጦርነቶች መካከል የ1ኛው እና የ2ተኛው ዓለም ጦርነቶች በዋነኛነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ የ1ኛው የዓለም ጦርነት በኃያላኑ የአውሮጳ አገራት መካከል እ.ኤ.አ ከ1906 እስከ 1911 ዓ.ም መግቢያ ድረስ ለአራት ዓመት የተደረገው ሲኾን በጦርነቱም አስራ አምስት ሚሊየን አውሮፓውያን ሕይወታቸውን ያጡበት ሆኖ ተመዝግቦ አልፏል፡፡ ሌላው ከ70 ሚሊየን ሕዝብ በላይ እንደቅጠል የረገፈበት እና በሂትለር ፊት አውራሪነት እ.ኤ.አ  ከ1932 ዓ.ም. እስከ 1937 ዓ.ም የተካሄደው የ2ተኛው ዓለም ጦርነት ነው፡፡ ታላላቅ የሚባሉትን ጦርነቶች ለማንሣት እንጂ ዓለማቸን ብዙ ሚሊየን ዜጎቿን የገበረችበት ጦርነቶች ተካሂደዋል፡፡ ጦርነት መነሻ ምክንያት ቢኖረውም መድረሻው ግን ውጤት አልባ ነው፡፡

  ከጦርነት ባልተናነሰ መልኩ በዓለማችን የሚነሡ ወረርሽኝ በሽታዎች የሰውን ልጅ ሕይወት በመቅጠፍ ግንባር ቀደምት ኾነው እናገኛቸዋለን፡፡ ከጥቁር ሞት (ቡቦኒክ) እስከ ንዳድ (ወባ)፣ ከስፓኒሽ (በአገራችን አጠራር የሕዳር በሽታ) እስከ ኤዥያን ፍሉ፣ ከፈንጣጣ እስከ ኩፍኝ፣ ከልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) እስከ ትክትክ፣  ከጂስቲንያን እስከ አንቶንያን ወረርሽኝ፣ ከኤች. አይ. ቪ.-ኤድስ እስከ ኢቦላ፣ ከሳርስ እስከ ኮሌራ፣ አሁን ደግሞ በዘመናችን የተከሰትው ኮሮናን ጨምሮ ከሦስት መቶ ስድሳ ስድስት ሚሊየን እስከ አራት መቶ አስራ አንድ ሚሊየን የሚደርስ የሰው ዘር ረግፋል እየረገፈም ይገኛል፡፡

  ታድያ እነዚህ የዘመናት የሰው ልጅ ፈተናዎች ግጭቶችና ወረርሽኞኝ ዝምድናቸው ምንድን ነው ቢሉ፡- ስማቸው በተጠራበት ቦታ ሞት ይነግሣል፣ነጻነት ይገሰሳል፣ራስወዳድነት ይገናል፣የመኖር ዋስተና ይጠፋል፣ ምጣኔ ሀብት ይደቃል፣ የትውለድ ቅብብሎሽ አደጋ ላይ ይወድቃል፣ በአጠቃላይ ሕይወት ትርጉም ያጣል፡፡

  በክርስቶስ ክርስትያን ለተባልን ሁላችን፡- በሥጋውያን መካከል የነበረውን የጥል ግርግዳ በመስቀሉ ላይ አፍርሶ፤ ጥልን ሽሮ፣ ሰላምን የሰጠን ሰላማችን እሱ ነውና (ኤፎ፤2÷ 14) ከጥላሻ ይልቅ መዋደድን፣ ከጠብ ይልቅ ፍቅርን፣ ከመጣል ይልቅ አብሮ መቆምን፣ ከመለያየት ይልቅ አንድነትን፣ በመካከላችን እናንግስ፡፡ ውሳጣዊ ሰላም የሚሰጠውን የሰላም አምላክ ይዘን፤ ከእግዚአብሔር ጋር የመኖር ጥበብ መንፈሳዊነትን እና ሰላምን ተላብሰን፤ ለምድራዊ ሕይወት ጥበብ ሥጋዊን ተጫምተን እንመላለስ፡፡ ጥበብ እግዚአብሔር ነውና በጥበብ እንኑር፡፡ ጥንቃቄ ይጋርዳልና ከባለሙያተኞች የሚሰጠንም ምክር እንስማ፡፡ በዓለማችን የተከሰተውን ወረርሽኝ ያርቅልን ዘንድ የስጋም የነፍስም መድኃኒት ወደሆነው አምላካችን በፀሎትና በምዕላ እንትጋ፡፡

  አበው እና ጠቢባኑ የሚሰጡትን ምክር እንተግብር !!!

  አምላክችን እግዚአብሔር ለዓለማችን ሰላምን ለሕሙማን ፈውስን ያድልልን !!!

   

  አባ ሳሙኤል

  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

  ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ

   https://www.facebook.com/EOTC.DICAC

    ©www.eotcdicac.org

   

  ‹ Back to List