Skip to main content

  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን 4.2 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ ለ 51 ገዳማት የምግብ እህል ገንዘብና የንጽህና እቃዎችን ለገሠ!! ABGELAUFEN SEIT 13.05.2020

  14.05.2020 Top news Media info
  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን 4.2 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ ለ 51 ገዳማት የምግብ እህል ገንዘብና የንጽህና እቃዎችን ለገሠ!!

  በአገሪቱ ላይ በጤና በደን ልማት ፣ሠላም፣ትምህርት፣ግብርና ሌሎች ዘርፈ ብዙ የመሠረተ ልማት መርሐ ግብሮች ላይ ከግማሽ ምእት ዓመት በላይ አጥጋቢ የልማት ሥራ ላይ ተሳትፎ ያለው ትልቅ ተቋም ነው፡፡

   በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በአገሪቱ ላይ በጤና በደን ልማት ፣ሠላም፣ትምህርት፣ግብርና ሌሎች ዘርፈ ብዙ የመሠረተ ልማት መርሐ ግብሮች ላይ ከግማሽ ምእት ዓመት በላይ አጥጋቢ የልማት ሥራ ላይ ተሳትፎ ያለው ትልቅ ተቋም ነው፡፡

  ✍️በአገር ውስጥ ያሉ ችግሮችን ፈጥኖ በመለይት ምላሽ መስጠት መለያው የሆነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በሀገራችን የተከሰተውን ወረርሽኝ በገዳማት ሊፈጥር የሚችለውን ችግር በመረዳት 4.2 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ገዳማዊ አባቶችን ከረሃብ ለመታደግ እየስራ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሣሙኤል ገልፀዋል፡፡
  በወረርሽኙ ምክንያት በሀገራችን ያሉት ገዳማት ከህዝቡ ያገኙት የነበረ በጉዞ ምክንያት በንግስ እንዲሁም በሱባኤ ምክንያት እየሄዱ ምዕመናን ባለመርዳታቸው ምክንያት በተጨማሪ በአለፈው የክረምት ወራት የዝናብ አጠር የሆኑ በቂ የሆነ ምርት ያልነበረባቸው ገዳማትና እንዲሁም ችግር ያለባቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ለእነዚህ ገዳማት እንደ ገዳማቱ ባህሪና ጸባይ እህል ገዝቶ እያከፋፈለ ይገኛል፡፡ በአንፃሩ በአካባቢው ያሉ ደሀ የሆኑ ሕብረተስቦች ጭምር የሚያሰፈልጋቸውን የእለት አቅርቦት በተለየ ምክንያት የተጎዱና የእለት ምግብ ያላገኙትንም ጭምር በመርዳት ለሚያስችል ስራ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

  97977341_166212148184264_625813487062351872_o
  ✍️የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሣሙኤል ገዳማውያኑ ከምግብ በአለፈ ለወረርሽኙ በቂ ግንዛቤ በመሥጠት ላይ እንደሆኑ ገልፀዋል፡፡በተለይ በወቅቱ በተፈጠረው ችግር ምክንያት ሰፋ ያለ ችግር ያለባቸው የእለት ልብስና ጉርስ ብቻ ሣይሆን አሁን ወቅቱ የግንዛቤም ጭምር በሽታ ምን አይነት በሽታ እንደሆነና በምን እንደሚተላለፍ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት እየሠጠን እንገኛለን በማለት አስረድተዋል፡፡

   

  96423319_166212168184262_7233465907106807808_n
  ✍️የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽነር አቶ ይልቃል ሽፈራው አሁን ወቅቱ የኮረና ቫይረስ ባስከተለው ችግር ምክንያት በተለይ ገዳማት ላይ በርካታ የሆኑ ችግሮች ተጋርጠዋል፡፡ ከሚል እሳቤ እንዲሁም በሽታው በባህሪው ከሚያስከትለው ሥነ ልቦናዊ፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች አንጻር ልማት ኮሚሽኑ ባለው አቅም ሁሉንም ገዳማት መርዳት ባይችልም አቅማችን በፈቀደው ወደ 51 የሚደርሱ ገዳማትን ለመደገፍ ሙከራ ተደርጓል፡፡የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ኮሚሽነር እንዳሉት ካሉ ብዙ ገዳማት መካከል 51 ገዳማትን እንዴት እደተመረጡ አስረድተዋል፡፡
  እንደገዳማቱ ባህሪ ጸባይ ጥቂት በሆኑት ገዳማት በራሳቸው መንቀሳቀስ ሰለሚችሉና ሊገዟቸው የሚችሉትን ለይተው ሰለሚያውቁ ቀጥታ ወደ አካውንታቸው እንዲገባ ተደርጓል፡፡ ነገር ግን 90 % የገዳማትን ዝርዝር እንደ ገዳማቱ ባህሪ አንዳንድ ገዳማት ላይ ቀይ ጤፍ ፣ማሽላ፣ በቆሎም፣ስንዴ፣ዳጉሳ የሚጠቀሙ ሲሆን አንዳንዶቹ ኑግና ተልባ ለማባያ የሚጠቅሙ ገዳማት አሉ፡፡ ከነዚህ ባህርያት አንጻር ገዳማቱ ባላቸው መናንያን ቁጥር መሠረት እርዳታው ከልማት ኮሚሽኑና ከሌሎች አካላት ጋር በመሆን ለ 51 ገዳማት ተደልድሎ ተግባራዊ እየሆነ ነው። በአጠቃላይ ኮሚሽኑ ለዚሁ ድጋፍ የሚሆን 4.2 ሚሊዮን ብር እንዳስተላለፉ አስረድተዋል፡፡
  www.eotcdicac.org

  https://www.facebook.com/EOTC.DICAC

  ‹ Back to List